ማቴዎስ 15:37-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ደቀ መዛሙርቱም የተረፈውን ቊርስራሽ ሰባት መሶብ ሙሉ አነሡ።

38. የበሉትም ከሴቶችና ከሕፃናት ሌላ አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።

39. ኢየሱስ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ በጀልባ ወደ መጌዶል ሄደ።

ማቴዎስ 15