ማርቆስ 8:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ጊዜ፣ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ ተሰበሰበ። የሚበሉት ምንም ምግብ ስላልነበራቸው ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፣ እንዲህ አላቸው፤

2. “ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ስለቈዩና የሚበሉትም ስለሌላቸው እነዚህ ሰዎች ያሳዝኑኛል፤

3. እንዲህ እንደ ተራቡ ወደ ቤታቸው ብሰዳቸው አንዳንዶቹ ከሩቅ የመጡ ስለሆኑ በመንገድ ላይ ዝለው ይወድቃሉ።”

ማርቆስ 8