3. እኔ የውዴ ነኝ፤ ውዴም የእኔ ነው፤መንጋውንም በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።
4. ውዴ ሆይ፤ አንቺ እንደ ቴርሳ የተዋብሽ፣እንደ ኢየሩሳሌም ያማርሽ፣ዐርማቸውን እንደ ያዙ ወታደሮችም ግርማን የተጐናጸፍሽ ነሽ።
5. አስጨንቀውኛልና፣እባክሽ ዐይኖችሽን ከእኔ ላይ አንሺ፤ጠጒርሽ ከገለዓድ ተራራ የሚወርድ፣የፍየል መንጋ ይመስላል።
6. ጥርሶችሽከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።