ማሕልየ መሓልይ 2:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኰይ፣ውዴም በጐልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።

4. ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው።

5. በዘቢብ አበረታቱኝ፤በእንኰይም አስደስቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና።

ማሕልየ መሓልይ 2