ሚክያስ 3:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤“እናንት የያዕቆብ መሪዎች፤እናንት የእስራኤል ቤት ገዦች ስሙ፤ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን?

2. መልካሙን ጠላችሁ፤ ክፉውንም ወደዳችሁ፤የሕዝቤን ቈዳ ገፈፋችሁ፤ሥጋቸውንም ከዐጥንቶቻቸው ለያችሁ፤

3. የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ፤ቈዳቸውን ገፈፋችሁ፤ዐጥንቶቻቸውንም ሰባበራችሁ፤በመጥበሻ እንደሚጠበስ፣በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቈራረጣችኋቸው።

ሚክያስ 3