ሚክያስ 2:11-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።

12. “ያዕቆብ ሆይ፤ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤በጒረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነትእሰበስባቸዋለሁ፤ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።

13. የሚሰብረው ወጥቶ በፊታቸው ይሄዳል፤እነርሱም በሩን በመስበር ወጥተው ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር እየመራቸው፣ንጉሣቸው ቀድሞአቸው ይሄዳል።

ሚክያስ 2