መዝሙር 98:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ አቅርቡ፤እርሱ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤ቀኝ እጁ፣ ቅዱስ ክንዱም፣ማዳንን አድርገውለታል።

2. እግዚአብሔር ማዳኑን አሳወቀ፤ጽድቁንም በሕዝቦች ፊት ገለጠ።

3. ለእስራኤል ቤት ምሕረቱን፣ታማኝነቱንም አሰበ፤የምድር ዳርቻዎችም ሁሉ፣የአምላካችንን ማዳን አዩ።

መዝሙር 98