መዝሙር 96:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ክብርና ግርማ በፊቱ ናቸው፤ብርታትና ውበትም በመቅደሱ ውስጥ አሉ።

7. የሕዝቦች ወገኖች ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ስጡ፤ክብርንና ብርታትን ለእግዚአብሔር ስጡ።

8. ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር ስጡ፤ቍርባንን ይዛችሁ ወደ አደባባዩ ግቡ።

9. በተቀደሰ ውበት ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ምድር ሁሉ፤ በፊቱ ተንቀጥቀጡ።

መዝሙር 96