መዝሙር 92:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ምሕረትህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማወጅ መልካም ነው፤

3. ዐሥር አውታር ባለው በገና፣በመሰንቆም ቅኝት ታጅቦ ማወጅ ጥሩ ነው።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ በሥራህ ስለ ተደሰትሁ፣ስለ እጅህ ሥራ በደስታ እዘምራለሁ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ታላቅ ነው!ሐሳብህስ ምን ያህል ጥልቅ ነው!

6. ደነዝ ሰው ይህን አያውቅም፤ነኁላላም አያስተውለውም።

መዝሙር 92