መዝሙር 91:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።

2. እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

3. እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ፣ከአሰቃቂ ቸነፈር ያድንሃልና።

መዝሙር 91