መዝሙር 90:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።

7. በቊጣህ አልቀናልና፤በመዓትህም ደንግጠናል።

8. በደላችንን በፊትህ፣የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ።

9. ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

መዝሙር 90