5. ሕዝቦችን ገሠጽህ፤ ክፉዎችንም አጠፋህ፤ስማቸውንም እስከ ወዲያኛው ደመሰስህ።
6. ጠላቶች ለዘላለም ጠፉ፤ከተሞቻቸውንም ገለባበጥሃቸው፤መታሰቢያቸውም ተደምስሶአል።
7. እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤መንበሩንም ለፍርድ አጽንቶአል።
8. ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።
9. እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።
10. ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።