መዝሙር 86:11-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤በእውነትህም እሄዳለሁ፤ስምህን እፈራ ዘንድ፣ያልተከፋፈለ ልብ ስጠኝ።

12. ጌታ አምላኬ ሆይ፤ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፤ስምህንም ለዘላለም አከብራለሁ፤

13. ለእኔ ያሳየሃት ምሕረት ታላቅ ናትና፤ነፍሴንም ከሲኦል ጥልቀት አውጥተሃል።

14. አምላክ ሆይ፤ እብሪተኞች ተነሥተውብኛል፤የዐመፀኞችም ጉባኤ ነፍሴን ይሿታል፤አንተንም ከምንም አልቈጠሩም።

15. ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ለቊጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።

መዝሙር 86