መዝሙር 80:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ለራስህ ባበረታኸው የሰው ልጅ ላይ፣በቀኝ እጅህ ሰው ላይ እጅህ ትሁን።

18. ከእንግዲህ አንተን ትተን ወደ ኋላ አንመለስም፤ሕያዋን አድርገን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን።

19. የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ መልሰን፤እንድንም ዘንድ፣ፊትህን አብራልን።

መዝሙር 80