መዝሙር 8:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. የጣቶችህን ሥራ፣ሰማያትህን ስመለከት፣በስፍራቸው ያኖርሃቸውን፣ጨረቃንና ከዋክብትን ሳይ፣

4. በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?

5. ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤የክብርንና የሞገስን ዘውድ አቀዳጀኸው።

6. በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛህለት፤

7. በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣የዱር አራዊትንም፣

8. የሰማይ ወፎችንና፣የባሕር ዓሦችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።

9. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊ ነው!

መዝሙር 8