መዝሙር 72:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤

2. እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

3. ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

4. ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል፤የድኾችን ልጆች ያድናል፤ጨቋኙንም ያደቀዋል።

5. ፀሓይ እስካለች ድረስ፣ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ፣ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።

መዝሙር 72