መዝሙር 72:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትህን ለንጉሥ፣ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤

2. እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

3. ተራሮች ብልጽግናን፣ኰረብቶችም የጽድቅን ፍሬ ለሕዝቡ ያመጣሉ።

መዝሙር 72