መዝሙር 70:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ታድነኝ ዘንድ ዘንበል በል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔን ለመርዳት ፍጠን።

2. ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ፣ይፈሩ፤ ሁከትም ይምጣባቸው፤ የእኔን መጐዳት የሚመኙ፣በውርደት ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

3. በእኔ ላይ፣ “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ፣ተሸማቀው ወደ ኋላ ይመለሱ።

መዝሙር 70