መዝሙር 7:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!

7. የሕዝቦች ጉባኤ ይክበብህ፤አንተም ከላይ ሆነህ ግዛቸው፤

8. እግዚአብሔር በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል። እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ጽድቄ ፍረድልኝ፤ልዑል ሆይ፤ እንደ ቅን አካሄዴ መልስልኝ።

9. ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ጻድቅ አምላክ ሆይ፤የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ጻድቁን ግን አጽና።

10. ጋሻዬ ልዑል አምላክ ነው፤እርሱ ልበ ቅኖችን ያድናቸዋል።

መዝሙር 7