መዝሙር 69:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. በጩኸት ደከምሁ፤ጉሮሮዬም ደረቀ፤አምላኬን በመጠባበቅ፣ዐይኖቼ ፈዘዙ።

4. ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ፣ከራሴ ጠጒር በዙ፤ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልጉ፣በከንቱም የሚጠሉኝ ብዙዎች ሆኑ፤ያልሰረቅሁትን ነገር፣መልሰህ አምጣ ተባልሁ።

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤በደሌም ከአንተ የተሰወረ አይደለም።

6. ጌታ የሰራዊት አምላክ ሆይ፤አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣በእኔ ምክንያት አይፈሩ፤የእስራኤል አምላክ ሆይ፤አንተን አጥብቀው የሚሹ፣ከእኔ የተነሣ አይዋረዱ።

7. ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፤እፍረትም ፊቴን ሸፍኖአልና።

መዝሙር 69