መዝሙር 68:29-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. በኢየሩሳሌም ስላለው ቤተ መቅደስህ፣ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡልሃል።

30. በሸምበቆ መካከል ያሉትን አራዊት፣በሕዝቡ ጥጆች መካከል ያለውንም የኮርማ መንጋ ገሥጽ፤ብር ይገብር ዘንድም ይንበርከክ፤ጦርነትን የሚወዱ ሕዝቦችንም በትናቸው።

31. መኳንንት ከግብፅ ይመጣሉ፤ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

32. የምድር መንግሥታት ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ለጌታ ተቀኙ። ሴላ

መዝሙር 68