መዝሙር 67:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ለሕዝቦች በቅን ስለምትፈርድላቸው፣ሰዎችንም በምድር ላይ ስለምትመራ፣ሕዝቦች ደስ ይበላቸው፤ በእልልታም ይዘምሩ። ሴላ

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።

6. ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል።

7. እግዚአብሔር ይባርከናል፤የምድርም ዳርቻዎች ሁሉ እርሱን ይፈሩታል።

መዝሙር 67