መዝሙር 66:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፤ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው!ጠላቶችህ ከኀይልህ ታላቅነት የተነሣ፣በፊትህ ይርዳሉ።

4. ምድር ሁሉ ይሰግድልሃል፤በዝማሬ ያመሰግኑሃል፤ለስምህም ይዘምራሉ። ሴላ

5. ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩበሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!

6. ባሕሩን የብስ አደረገው፤ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ኑ፣ በእርሱ ደስ ይበለን።

7. በኀይሉ ለዘላለም ይገዛል፤ዐይኖቹ ሕዝቦችን ይመለከታሉ፤እንግዲህ ዐመፀኞች ቀና ቀና አይበሉ። ሴላ

8. ሕዝቦች ሆይ፤ አምላካችንን ባርኩ፤የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።

9. እኛን በሕይወት የሚያኖረን፣እግራችንንም ከመንሸራተት የሚጠብቅ እርሱ ነው።

መዝሙር 66