መዝሙር 66:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. አምላክ ሆይ፤ አንተ ፈተንኸን፤እንደ ብርም አነጠርኸን።

11. ወደ ወጥመድ አገባኸን፤በጀርባችንም ሸክም ጫንህብን።

12. ሰዎች በራሳችን ላይ እንዲፈነጩ አደረግህ፤በእሳትና በውሃ መካከል አለፍን፤የኋላ ኋላ ግን ወደ በረከት አመጣኸን።

13. የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ስእለቴንም ለአንተ እፈጽማለሁ፤

14. በመከራ ጊዜ ከአፌ የወጣ፣በከንፈሬም የተናገርሁት ስእለት ነው።

መዝሙር 66