መዝሙር 61:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ጸሎቴንም አድምጥ።

2. ልቤ በዛለ ጊዜ፣ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።

3. አንተ መጠጊያዬ፣ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና።

4. በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ

5. አምላክ ሆይ፤ ስእለቴን ሰምተሃልና፤ስምህን የሚፈሩትንም ሰዎች ርስት ለእኔ ሰጠህ።

መዝሙር 61