መዝሙር 60:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጣልኸን፤ አንኰታኰትኸን፤ተቈጣኸንም፤ አሁን ግን መልሰህ አብጀን።

2. ምድሪቱን አናወጥሃት፤ ፍርክስክስ አደረግሃት፤ትንገዳገዳለችና ስብራቷን ጠግን።

3. ለሕዝብህ አበሳውን አሳየኸው፤ናላ የሚያዞር የወይን ጠጅ እንድንጠጣም ሰጠኸን።

4. ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ

መዝሙር 60