መዝሙር 59:6-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. እንደ ውሻ እያላዘኑ፣በምሽት ተመልሰው ይመጣሉ፤በከተማዪቱም ዙሪያ ይራወጣሉ።

7. ከአፋቸው የሚወጣውን ተመልከት፤ሰይፍ በከንፈራቸው ላይ አለ፤“ማን ሊሰማን ይችላል?” ይላሉና።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ሕዝቦችን ሁሉ በንቀት ታያቸዋለህ።

9. ብርታቴ ሆይ፤ አንተን እጠብቃለሁ፤አምላክ ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህና።

መዝሙር 59