መዝሙር 59:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ ከጠላቶቼ እጅ አድነኝ፤ሊያጠቁኝ ከሚነሡብኝም ጠብቀኝ።

2. ከክፉ አድራጊዎች ታደገኝ፤ደም ከተጠሙ ሰዎችም አድነኝ።

3. እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴበላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ።

መዝሙር 59