መዝሙር 56:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣እምነቴን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

4. ቃሉን በማመሰግነው አምላክ፣በእግዚአብሔር ታምኛለሁ፤ አልፈራም፤ሥጋ ለባሽ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

5. ቀኑን ሙሉ ቃሌን ያጣምሙታል፤ዘወትርም ሊጐዱኝ ያሤራሉ።

6. ይዶልታሉ፤ ያደባሉ፤ርምጃዬን ይከታተላሉ፤ነፍሴንም ለማጥፋት ይሻሉ።

7. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከቶ እንዳያመልጡ፣ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።

መዝሙር 56