መዝሙር 55:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ልቤ በውስጤ ተጨነቀብኝ፤የሞት ድንጋጤም በላዬ መጣ።

5. ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ሽብርም ዋጠኝ።

6. እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ!በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤

7. እነሆ፤ ኰብልዬ በራቅሁ፣በምድረ በዳም በሰነበትሁ ነበር፤ ሴላ

8. ከዐውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼ፣ወደ መጠለያዬ ፈጥኜ በደረስሁ ነበር።”

መዝሙር 55