መዝሙር 49:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. እግዚአብሔር ግን ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል፤በርግጥም በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለኝ። ሴላ

16. ሰው ባለጠጋ ሲሆን፣የቤቱም ክብር ሲበዛለት አትፍራ፤

17. በሚሞትበትም ጊዜ ይዞት የሚሄደው አንዳች የለምና፤ክብሩም አብሮት አይወርድም።

መዝሙር 49