መዝሙር 45:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።

3. ኀያል ሆይ፤ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ፤ግርማ ሞገስንም ተላበስ።

4. ስለ እውነት፣ ስለ ትሕትና ስለ ጽድቅ፣ሞገስን ተጐናጽፈህ በድል አድራጊነት ገሥግሥ፤ቀኝ እጅህም ድንቅ ተግባር ታሳይ።

5. የሾሉ ፍላጻዎችህ በንጉሥ ጠላቶች ልብ ይሰካሉ፤ሕዝቦችም ከእግርህ በታች ይወድቃሉ።

መዝሙር 45