መዝሙር 44:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤አንተ ወደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።

4. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ንጉሤ ነህ፤ያዕቆብም ድል እንዲያደርግ የወሰንህ አንተ ነህ።

5. በአንተ ጠላቶቻችን በመጡበት እንዲመለሱ እናደርጋለን፤በስምህም ባላጋራዎቻችንን ከእግራችን በታች እንረግጣለን።

6. በቀስቴ አልተማመንም፤ሰይፌም አያስጥለኝም።

መዝሙር 44