መዝሙር 44:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ?ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።

24. ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?መከራችንንና መጠቃታችንን ለምን ትረሳለህ?

25. ነፍሳችን ዐፈር ውስጥ ሰጥማለች፤ሆዳችንም ከምድር ጋር ተጣብቆአል።

26. ተነሥና እርዳን!ስለ ምሕረትህ ስትል ተቤዠን።

መዝሙር 44