መዝሙር 44:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አምላክ ሆይ፤ በጆሮአችን ሰምተናል፤አባቶቻችን በቀድሞ ዘመን፣እነርሱ በነበሩበት ዘመን፣ያደረግኸውን ነግረውናል።

2. ሕዝቦችን በእጅህ አሳደህ አወጣሃቸው፤አባቶቻችንን ግን ተከልሃቸው፤ሕዝቦችን አደቀቅህ፤አባቶቻችንን ግን ነጻ አወጣሃቸው።

3. ምድሪቱን የወረሱት በሰይፋቸው አልነበረም፤ድልንም የተጐናጸፉት በክንዳቸው አይደለም፤አንተ ወደሃቸዋልና ቀኝ እጅህ፣ክንድህና የፊትህ ብርሃን ይህን አደረገ።

መዝሙር 44