መዝሙር 40:15-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. በእኔ ላይ፣ “እሰይ! እሰይ!” የሚሉ፣በራሳቸው እፍረት ይደንግጡ።

16. አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስ ይበላቸው፤ዘወትር የአንተን ማዳን የሚወዱ፣ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል” ይበሉ።

17. እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝ፤ጌታ ግን ያስብልኛል።አንተ ረዳቴና አዳኜ ነህ፤አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ።

መዝሙር 40