መዝሙር 39:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ

6. ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤በከንቱም ይታወካል፤ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።

7. “ጌታ ሆይ፤ አሁንስ ወደ ማን ልመልከት?ተስፋዬ በአንተ ላይ ነው።

8. ከኀጢአቴ ሁሉ አድነኝ፤የሰነፎች መሣለቂያ አታድርገኝ።

9. ይህን ያደረግህ አንተ ነህና፣ዝም እላለሁ፤ አፌንም አልከፍትም።

መዝሙር 39