መዝሙር 39:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ልቤ በውስጤ ጋለ፤በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤

4. “እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤አላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።

5. እነሆ፤ ዘመኔን በስንዝር ለክተህ አስቀመጥህ፤ዕድሜዬም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው፤በእርግጥ የሰው ሁሉ ሕይወት ተን ነው። ሴላ

መዝሙር 39