መዝሙር 38:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ብርቱዎች ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤ያለ ምክንያት የሚጠሉኝም ስፍር ቊጥር የላቸውም።

20. መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ጠሉኝ።

21. እግዚአብሔር ሆይ፤ አትተወኝ፤አምላኬ ሆይ፤ ከእኔ አትራቅ።

22. ጌታዬ መድኅኔ ሆይ፤እኔን ለመርዳት ፍጠን።

መዝሙር 38