መዝሙር 33:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል፤ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።

6. በእግዚአብሔር ቃል ሰማያት ተሠሩ፤በአፉም እስትንፋስ የከዋክብት ሰራዊት።

7. የባሕርን ውሃ በአንድ ዕቃ ይሰበስባል፤ቀላዩንም በአንድ ስፍራ ያከማቻል።

8. ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፤በዓለም የሚኖር ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ።

9. እርሱ ተናግሮአልና ሆኑ፤አዞአልና ጸኑም።

መዝሙር 33