መዝሙር 32:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መተላለፉ ይቅር የተባለለት፣ኀጢአቱም የተሸፈነለት፣እንዴት ቡሩክ ነው!

2. እግዚአብሔር ኀጢአቱን የማይቈጥርበት፣በመንፈሱም ሽንገላ የሌለበት ሰው፣እርሱ ቡሩክ ነው።

3. ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ዝም ባልሁ ጊዜ፣ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤

4. በቀንና በሌሊት፣እጅህ ከብዳብኛለችና፤ኀይሌም የበጋ ትኵሳት እንደላሰው ነገር፣ከውስጤ ተሟጠጠ። ሴላ

መዝሙር 32