መዝሙር 31:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. አንተ መጠጊያዬ ነህና፣በስውር ከተዘረጋብኝ ወጥመድ አውጣኝ።

5. መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤አንተ ተቤዠኝ።

6. ለከንቱ ጣዖታት ስፍራ የሚሰጡትን ጠላሁ፤ነገር ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ።

7. በምሕረትህ ደስ እሰኛለሁ፤ ሐሤትም አደርጋለሁ፤መከራዬን አይተሃልና፤የነፍሴንም ጭንቀት ዐውቀሃል።

መዝሙር 31