መዝሙር 30:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከታች አንሥተኸኛልና፣ጠላቶቼም በላዬ እንዳይደሰቱ አድርገሃልና፣ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

2. እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ትረዳኝ ዘንድ ወደ አንተ ጮኽሁ፤አንተም ፈወስኸኝ።

3. እግዚአብሔር ሆይ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፤ወደ ጒድጓድ ከመውረድም መልሰህ ሕያው አደረግኸኝ።

4. እናንተ ቅዱሳኑ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ቅዱስ ስሙንም አወድሱ።

መዝሙር 30