መዝሙር 28:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤አንተ ዝም ካልኸኝ፤ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።

2. ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣የልመናዬን ቃል ስማ።

3. በልባቸው ተንኰል እያለ፣ከባልንጀሮቻቸው ጋር በሰላም ከሚናገሩ፣ከክፉ አድራጊዎችና፣ከዐመፃ ሰዎች ጋር ጐትተህ አትውሰደኝ።

መዝሙር 28