መዝሙር 26:3-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣በእውነትህም ተመላለስሁ።

4. ከማይረቡ ጋር አልተቀመጥሁም፤ከግብዞችም ጋር አልተባበርሁም።

5. የክፉዎችን ማኅበር ተጸየፍሁ፤ከዐመፀኞችም ጋር አልቀመጥም።

መዝሙር 26