መዝሙር 25:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የልጅነቴን ኀጢአት፣መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣እንደ ምሕረትህም መጠን ዐስበኝ።

8. እግዚአብሔር መልካምና ቅን ነው፤ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።

9. ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።

10. ኪዳኑንና ሥርዐቱን ለሚጠብቁ፣ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።

11. እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአቴ ታላቅ ነውና፣ስለ ስምህ ይቅር በልልኝ።

12. እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው?በተመረጠለት መንገድ ያስተምረዋል።

መዝሙር 25