መዝሙር 25:19-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።

20. ነፍሴን ጠብቃት፤ ታደገኝም፤መጠጊያዬ ነህና አታሳፍረኝ።

21. አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና፣ታማኝነትና ቅንነት ይጠብቁኝ።

22. አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን፣ከመከራው ሁሉ አድነው።

መዝሙር 25