መዝሙር 21:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. መልካም በረከት ይዘህ በመንገዱ ላይ ጠብቀኸው፤የንጹሕ ወርቅ ዘውድም በራሱ ላይ ደፋህለት።

4. ሕይወትን ለመነህ፤ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።

5. ባቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ክብርንና ሞገስን አጐናጸፍኸው።

6. ዘላለማዊ በረከትን ሰጠኸው፤ከአንተ ዘንድ በሚገኝ ፍስሓም ደስ አሰኘኸው፤

መዝሙር 21