መዝሙር 18:26-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. ከንጹሑ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ለጠማማው አንተ ትጠምበታለህ።

27. አንተ ትሑታንን ታድናለህ፤ትዕቢተኛውን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።

28. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መብራቴን ታበራለህ፤አምላኬ ሆይ፤ ጨለማዬን ብርሃን ታደርገዋለህ።

29. በአንተ ጒልበት በሰራዊት ላይ እረማመዳለሁ፤በአምላኬም ኀይል ቅጥር እዘላለሁ።

30. የአምላክ መንገድ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው።መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣እርሱ ጋሻ ነው።

መዝሙር 18