መዝሙር 17:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. አምላክ ሆይ፤ ስለምትመልስልኝ አንተን እጣራለሁ፤ጆሮህን ወደ እኔ ጣል አድርገህ ጸሎቴን ስማ።

7. ከጠላቶቻቸው መተገኛ ያደረጉህን፣በቀኝ እጅህ የምትታደግ ሆይ፤ጽኑ ፍቅርህን ድንቅ አድርገህ ግለጥ።

8. እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤

9. ከሚያስጨንቁኝ ከክፉዎች፣ከሚከብቡኝ አደገኛ ባላንጣዎቼ ጋርደኝ።

10. ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ።

መዝሙር 17